Home > Tribute > Tribute to a Patriarch (Amahric text)

Tribute to a Patriarch (Amahric text)

September 28, 2012 Leave a comment Go to comments

The head of the Ethiopian Orthodox Church, Abune Paulos, has died aged 76, in mid-august. In the following Amharic article sent to Addis Journal, a journalist for the church’s official paper, Dereje Tizazu reflects about the patriarch’s life.

(photo by Aida Muluneh)

ጥቁር ቀን
ጥቁር ቀን፡፡ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት፡፡ ከጥቁር ሰማይ የሚወርደው ካፊያ ጥቋቁር የለበሰውን ምእመናንን በስሱ ያረሰርሰዋል፡፡ በሀዘን መደራረብ ውስጡ የታመመው ምእመን እንደ እለቱ ሁሉ ስሜቱ ጥቁር ነው፡፡
እነሆ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ለቅዱስነታቸው አስከሬን የመጨረሻ ሽኝት የተገኘው ምእመን በጠቆረ ስሜት ውስጥ ሆኖ የሽኝቱን መርሃ ግብር በጥሞና ይከታተላል፡፡ እኔም በአውደ ምህረቱ አንድ ጥግ ሆኜ በትንሽ ማስታወሻ ደብተር በጥቁር ብዕሬ በጥቋቁር ቃላት ጥቋቁር አረፍተ ነገሮችን አነጥባለሁ፡፡
ለዘመናት ለምእመናን ቃለ እግዚአብሔር ያስተምሩበት፣ምእመናንን ይባርኩበት፣ፀሎት ያደርሱበት የነበረው አውደ ምህረት ላይ ዛሬ የሉም፡፡ አውደ ምህረቱ ለአስከሬናቸው ሽኝት በተገኙ ምእመናን እና ሀዘንተኛ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተጣቧል፡፡
ከአውደ ምህረቱ ትይዩ ለሕዝብ እይታ ምቹ በሆነ ቦታ ባንዲራ ለብሶ በብልጭልጭ ተከፍኖ የሚታየው አስከሬን ይባስ የውስጥን ህመም ያበረታል፡፡
የሽኝቱ መርሀ ግብር አጠር አጠር እየተደረገ አንዳንዱም እየተዘለለ ቀጥሏል፡፡
ጋዜጠኛ ይራወጣል፡ሕዝቡም በግል ካሜራውና በሞባይሉ ታሪክን ለማኖር የራሱን ጥረት ያደርጋል፡፡
ግፊያው፣ትርምሱ ለጉድ ነው፡፡መቆሚያ መቀመጫ በታጣለት አውደ ምህረት አካባቢ እንደሌላው ግዜ ለጀግናው ኃይሌ ገብረሥላሴ ልዩ የክብር ቦታ የሰጠው የለም፡፡ እርሱም ይህን አልፈለገም፤እንደኛው እትርምሱ መሀል ብዙ ቆሟል፡፡ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅም ትንሽ ማረፊያ ያገኙ ዘንድ ወዲያ ወዲህ ለማለት እንኳ አልተቻላቸውም፡፡ከውጭ የመጡ እንግዶችም ቆመው መርሀ ግብሩን መከታተል ግድ ብሏቸዋል፡፡ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣አረጋውያን፣ካህናት አባቶችና እቅመ ደካማ እናቶችም እንደዚሁ ብዙ ሲደክሙ አስተዋልኩ፡፡ ወይ ዛሬ!

በመርሀ ግብሩ መሰረት የቅዱስነታቸው የህይወት ታሪክ ባጭሩ ሲነበብ ብዙ ደቂቃዎችን ወስዷል፡፡የቅዱስነታቸው የመጨረሻ ወንድም ስለ ቅዱስነታቸው ማንነት ጥቂት ሲናገሩ ከመርሀ ግብሮቹ አብላጫውን ደቂቃዎች ተጠቅመዋል፡፡ በቅጥረ ግቢው በብቸኝነት ነጭ የለበሱት ካህናት ያቀረቡት ቀዝቃዛ ወረብ እንደ ሌላው ግዜ ቀልብ አልገዛም፡፡በአስከሬኑ ዙሪያ የአሀት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በየራሳቸው ቋንቋ ያደረሱት አጭር ፀሎት ‘ቶሎ ባለቀ’ የሚያስብል አልነበረም፡፡
ከአለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ተወካይ ጀምሮ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት እና የአምስቱ አሀት ቤተክርስቲያን የሀዘን መግለጪያ በየተራ ሲነበብ ሕዝቡ አልተሰላቸም፡፡ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣናትም በአጭር በአጭር ያቀረቡት የሀዘን መግለጪያ ልብ የሚነካ ነው፡፡
እነሆ በስጋ ሞት የተለዩን ቅዱስ አባታችን የመጨረሻ ሽኝት ወቅት ቀስ በቀስ ሰማዩ እየገፈፈ ጥቁረቱን ቢለቅም የሕዝቡ ስሜት ግን አሁንም እንደ አልባሳቱ ሁሉ የጠቋቆረ ነው፡፡አጠገቤ በዝምታ የሚያነቡ እናት ሆዴን አባቡት፡፡ከወደ ኋላዬ በታፈነ ድምፅ የሚስረቀረቁት አባት ይባስ አስከፉኝ፡፡
እኔም በጠቋቆረ ስሜቴ ስለ ቅዱስ አባታችን ጥቂት ለማሰብ ስሞክር ብዙ ትዕይንቶች በአይነ ህሊናዬ መሰስ እያሉ ማለፍ ጀመሩ፡፡ የቅዱስነታቸው ተክለ ሰውነት፣ክብራቸው፣ግርማቸው፣ድምፃቸው እና ሌሎች ሁኔታዎቻቸው በብዙ ሁለንተናዬን ገዝተው ከመርሀ ግበሩ አስወጡኝ፡፡
ላለፉት አራት አመታት እርሳቸው በተገኙባቸው እና ለዘገባ አስፈላጊ በሆኑ ክስተቶች ላይ ተገኝቶ የመዘገብ እድል ያገኘሁባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ነበሩ፡፡ በመንበራቸው ሆነው ያንቀላፉ በመመሰል አይናቸውን ጨፈን በማድረግ በአርምሞ የመቆየታቸው ነገር፣በነገሮች ሲገረሙ ትንሽ ለቀቅ አደርገው መለስ የሚያደርጓት ፈገግታቸው፣በንግግራቸው አፅንኦት ለመስጠት ለሚፈልጉት ጉዳይ የመጨረሻውን ቃል ለአራት ነጥብ እንደሚመች ረገጥ አድርገው የመናገራቸውን ሁኔታ አሰብኩ፡፡
ምእመኑ ከእርሳቸው ቡራኬ ለማግኘት እና መስቀል ለመቀበል ሲል በዙሪያቸው በሚያስተዋለው ግፊያና ትርምስ መሀል ያለብስጭት ሲያልፉ ታዩኝ፡፡ ለቅዱስነታቸው ክብር በሰንበት ትምህርተ ቤቶች ህብረ ድምፅ የሚዘመረው መዝሙር በውስጤ ተሰማኝ፡፡ “ ኦዎዎዎ አባ ቅዱስ …” ለተለያዩ አመት በዓላት ዋዜማ የመልካም ምኞት መግለጪያ ሲሰጡ በተገኘሁበት ጥቂት አጋጣሚዎች ለበረከት ብለው ለጋዜጠኞች የሚለግሱት ብር እና ሌላ ሌላም ታሰበኝ፡፡ የቅዳሴ ስርአትን ሲመሩ የብቃታቸውን መጨረሻና የድምፃቸው ማማር፣ሌላውን ዓለምም የሚያስደምመው የእንግሊዚኛ ቋንቋ ችሎታቸውና ስብከታቸው እንዲሁም የዲፕሎማሲያዊ ጥበባቸው በብዙ አስደመመኝ፡፡
እነሆ በዚህ ጥቁር ቀን፤ ከዚህ ጥልቅ ሀሳቤ ያናጠቡኝ የቅዱስነታቸው አስከሬን ግብአተ መሬት ተፈፅሞ መርሀ ግብሩን በፀሎት ሊያሳርጉ በድምፅ ማጉያ ሕዝቡ ከበረታ ሀዘኑ፣ከእሪታና ጩኸቱን እንዲታገስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በጠየቁ ግዜ ነው፡፡
ቅዱስነታቸው በሕይወት በነበሩበት ዘመናት እርሳቸው ያሰቡትን እና ያለሙትን ፈፅመው አልፈዋል፡፡ በሃይማኖታዊ ስልጣናቸውም የወደዱትን አድርገዋል፡፡ ስለ እርሳቸው የተለያዩ ወገኖች የተለያየ አመለካከት ሊኖራቸው ይቸላል፡፡ በዚህ ስርአተ ቀብራቸው ላይ ያንን ማሰብ አልወደድኩም ግን ቸሩ እግዚአብሔር በፍሳቸውን በገነት እንዲያኖር ተመኘሁ፡፡
ሰው ሕይወት አለው፤ህይወት ያለው ሁሉ ይሞታል፡፡ቅዱስ አባታችን አቡነ ዻውሎስ ሰው ናቸው ፡፡ስለዚህ ይሞታሉ፡፡ ሞተዋልም፡፡
አከውደ ምህረቱ ትይዩ ባረፈው አስከሬናቸው ላይ ክምር የአበባ ጉንጉን የታየኝ በግቤው ብዙ ቆይቼ ሰዉ ቀስ በቀስ ወደ መጣበት ሲያመራና አካባቤው ለቀቅ ሲደረግ ነው፡፡ ሰው ከሞት በፊት እና ከትንሳኤ በኋላ በአንድ ዓለም ይኖራል፡፡ ከሰዓተ ሞት እስከ ሰዓተ ትንሣኤ ግን የሚኖረው በሁለት ዓለም ነው፡፡በመሆኑም ሥጋው በዚህ ዓለም እግዚአብሔር በወሰነው ቦታና ሁኔታ ትኖራለች፡፡ ይህ ጥቅስ ትዝ አለኝ፡፡“ኩሉ ኮነ በፈቃደ እግዚአብሔር…”
ጥቁር ስሜት ውስጥ ሆኜ ዖሙን ልንፈታ ከአንድ ወዳጄ ጋር ወደተቀጣጠርንበት በዝግታ ሳዘገም ይህ ጥቁር ቀን ቶሎ ያልፍ ዘንድ በመመኘት ነበር፡፡
(ደረጀ ትዕዛዙ

Advertisements
 1. September 28, 2012 at 2:13 pm

  Thanks Dere and Addis Journal for sharing this sweet piece with us, good figures of speech and nice angle. I also like the fact that the piece is free from bias, he showed me what he had seen on the funeral day!

 2. kitcho
  September 29, 2012 at 6:06 pm

  Time indeed has changed in the Orthodox church. We had a gun packing Abuna, installed to the position, just because if ethnicity as well as, being a supporter of genocide, just like the pope in Rome at the time of the WWII. Not only that, his lavish life style indeed disqualify to be a rough priest, who never ever have served in the church. It is amazing. i guess, some people do deserve to die and no one should mourn such type of people, which this dude was one. God ridden

 3. emebet
  September 29, 2012 at 6:32 pm

  It´s good journalistic view and observation. 10q for shearing us.

 1. No trackbacks yet.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: